ድህነት እና ምግባር

AreWeGoodEnoughForLiberty?በ1989ዓ/ም(እኤአ) አሁን በሕይወት የማይገኝ ጓደኛዬ ዶ/ር ሃይንግ ንጎር ማለትም “The Killing Fields“ በተባለው ፊልም ውስጥ በነበረው ሚና የ Academia Award አሸናፊ ከነበረው ጋር ወደ ካምቦዲያ ተጓዝኩ፡፡ በወቅቱ ካምቦዲያ ዋና ከተማ ፍኖምፔን ውስጥ ለሚገኝ አንድ ሆስፒታል ለማስረከብ የምንወስደውን በእርዳታ የተገኙ የህክምና ቁሳቁሶች በማዘጋጀት ላይ ስለነበርኩ ከጉዞው ቀደም ብሎ ከፍተኛ የሀገር ውስጥ የፕሬስ ትኩረት አግኝተን ነበር።

በፕሬስ የዜናውን ታሪክ የተከታተለች ሻሮን ሃርትሊን የተባለች ሴት በወቅቱ ከክሜር ሩዥ ኮምዩኒስቶች የግፍ አገዛዝ አምልጠው እኔ እኖርበት በነበረው የሚችጋን ግዛቷ ሚድላንድ ከተማ ውስጥ ኑሮ ለጀመሩ የካምቦዲያዊያን ቤተሰቦች  ካምቦዲያ ላሉ ዘመዶቻቸው ከገንዘብ ጋር የታሸጉ ደብዳቤዎችን እንዳደርስላቸው ፈቃደኝነቴን ጠየቀችኝ፡፡ እኔም ፈቃደኛ መሆኔን በመግለጽ በውስጣቸው 200ዶላር ከደብዳቤ ጋር የታሸገባቸው ሶስት ፖስታዎችን ተቀበልኩ።

ሁለቱን ፖስታዎች የሚቀበሉት ሰዎች ይኖሩ የነበረው በዋና ከተማዋ ፍኖምፔን ሲሆን አንደኛው ፖስታ ተረካቢ ቤተሰብ ግን የበርካታ ኪሎሜትሮች ርቀት ላይ በምትገኝዋ በባታምባንግ በተባለ ስፍራ ነበር የሚኖሩት። ወደ ባታምባንግ የሚደረግ ጉዞ ደግሞ በባቡር መጓዝን ፣ ለሚደርሱ አደጋዎች ኃላፊነት መውሰድን እና ረዘም ያለ ጊዜን የሚጠይቅ ነው። ይህም ሆኖ ፓስታውን የሠጡኝ ሰዎች የፈለገው ነገር ቢከሰት ገንዘቡን ፈፅሞ ይዤ እንዳልመለስ ነግረውኛል፡፡ ቤተሰቦቻቸውን ማግኘት ባልችል እንኳ  ላጋጠመኝ ማንኛውም ደሃ ካምቦዲያዊ ገንዘቡን እንድሰጥ አሳስበውኛል። ካምቦዲያ ውስጥ ደግሞ ችግረኛ እና ደሃ የሆኑ ሰዎች በየስፍራው ሞልተዋል፡፡

ወደ ሀገር ቤት ለመመስ አንድ ቀን በቀረኝ ጊዜ  ገንዘቡን ለማድረስ ወደ ባታምባንግ መሔድ አለመቻሌን ስገነዘብ ባረፉኩበት ሆቴል አካባቢ ለበርካታ ጊዜ ደጋግሜ ወዳየሁት እና የተበጫጨቀ ልብስ ወደ ለበሰ አንድ ሰው ቀርብ ብየ አናገርኩ፡፡ ይህ ሰው በቂ እንግሊዘኛ መናገር በመቻሉም በደንብ ተግባብን፡፡ በዚያን ጊዜ እንደ ብዙሃኑ ካምቦዲያዊያን እሱም ምንም የሌለው ድሃ ነበር፡፡

“ከ200 ዶላር ጋር የታሸገ ደብዳቤ እጄ ላይ ይገኛል፡፡ በባታምባንግ ለሚገኝ አንድ ቤተሰብ የተላከ ነው፡፡ ማድረስ ከቻልክ 50ውን ዶላር ለድካምህ እና ለምታወጣው ወጪ ወስደህ ቀሪውን ለተላከላቸው ቤተሰብ እንድትሰጥልኝ እፈልጋለሁ፡፡” አልኩት፡፡ ፈቃዱን ገለፀልኝና የመሰናበቻ ሰላምታ ተለዋውጠን ተለያየን፡፡ ከዚያ በኋላ እሱም አድርስ ብየ የሰጠሁት ገንዘብ ከምን እንደሚደርሱ አንዳችም ነገር መስማት እንደማልችል ለራሴ ደመደምኩ፡፡

ከበርካታ ወራት በኋላ ሻሮን አስደሳች የሆነ የስልክ ጥሪ አደረገችልኝ፡፡ ሻሮን ወደ ባታምባንግ ገንዘብ ለዘመዶቻቸው የላኩት ሰዎች የጻፉላት ደብዳቤ እንደደረሳት ነገረችኝ፡፡ ደብዳቤውን በስልክ ስታነብልኝ  ዓይኖቼ ልገታው የማልችል የእንባ ዘለላዎችን አፈለቁ፡፡ ከደብዳቤውም ላይ “ለተላከልን 200 ዶላር እናመሰግናለን።” የሚለውን ጭምር አነበበችልኝ።

ያ ድሃ ሰው ወደ ባታምባንግ ሔዷል፡፡ የሚገርመው 50ውን ዶላር ለራሱ እንዲወስድ በግልፅ የነገርኩትን አለመውሰዱ ብቻ ሳይሆን ወደ ስፍራው ሲሔድ ለባቡር ጉዞ ከራሱ ኪስ 10 ዶላር ማውጣቱ ጭምር ነው፡፡ ምግባር ማለት ይህ ነው፡፡ ይህን ሰው ይበልጥ ማወቅና አድራሻውንም ፈፅሞ መጠየቅ ሳያስፈልገኝ ምናልባትም ሕይወቴን በሙሉ እንደዚህ ደሃ በመንፈስ እና በምግባር የላቀ ፋይዳ ያለው ገለሰብ ለመሆን እጥራለሁ።

የጽሁፉ ምንጭ: Are we good enough for Liberty? የተሰኘው እና በ2013 ለህትመት የበቃው የላውረንስ ሪድ መጽሃፍ ነው።

About these ads

Thank you for your comments

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s